ዋና ዋና ተግባር
የድርጅቱን ጋራዥ ሥራዎች ነከፍተኛ ኃላፊነት ያከናውናል፤ በሥሩ ያትን ሠራተኞች ያስተባብራል፣ የሥራ አፈጻጸማቸውን ይቆጣጠራል።
የሥራ መደቡ ዝርዝር ተግባራት
1. የጥገና ሥራዎችን ያቅዳል፣ ያቀናጃል፣ ይከታተላል፣ ያከናውናል፤
· የጥገና ሥራዎችን ያቅዳል፣ በቅደም ተከተል ለሥራ ያዘጋጃል፣ ለሥራ የሚያስፈልጉ የሰው ኃይልና መሣሪያዎችን ያደራጃል፣
· ከባድ ብልሽት ያጋጠማቸውን ተሽከርካሪዎች አድሶና ጠግኖ በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
· ተጠግነው በሥራ ላይ የማይውሉና ከሚሰጡት ጥቅም ወጪያቸው የሚበልጠውን ተሽከርካሪዎች በመለየት የሚወገዱበትን መንገድ አጥንቶ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣
· የጥገና ሥራ በቅደም ተከተል በማስቀመጥ በቅንጅት ለማከናወን በሥሩ ለተመደቡ መካኒኮች ሥራ ያከፋፍላል፣ አፈጻጸሙንም ይቆጣጠራል፣ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ይሞላል፣
· በአስቸኳይ ለሥራ የሚፈለጉ መሣሪያዎች በቅድሚያ በመጠገን ለሥራ ዝግጁ ያደርጋል፣
· ጋራዡ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲኖረው የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣
· የመጠባበቂያ አላቂ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ይይዛል፣ ከማለቃቸውም በፊት ተከታትሎ እንዲተኩ ያደርጋል፣
· በእቃ ግዥ ሠራተኞችና ከኃላፊዎች ጋር በመወያየት የሚገዙ መለዋወጫ ምን ዓይነት መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማል፣
· ጥገናዎች በድርጅቱ/ፕሮጀክቱ/ ጋራዥ ወይም ከድርጅቱ ውጪ መከናወናቸው የሚያስከትለውን ጥቅምና ጉዳት በመለየት፣ በቂ ጥገናና ተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበትን ጋራዥ በመምረጥ ይወስናል፣
· ተደጋጋሚ ብልሽቶችን መንስኤ በሚገባ በማጤን መፍትሄ ይሰጣል፣
· ጋራዡና አካባቢው ከአደጋ የራቀ መሆኑን ያረጋግጣል፣
o የመጠቀሚያ ቁሳቁሶች አደጋ በማያስከትል ሁኔታ መቀመጣቸውን፣
o እሳት የሚያስነሱ ወይም ተቀጣጣይ ነገሮች በጥንቃቄ መቀመጣቸውን፣
o የእሳት ማጥፊያ ለአደጋ በተጋለጡ ቦታዎች መኖሩን በማረጋገጥ
· የተጠገኑ መኪናዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ ከመደረጋቸው በፊት ይፈትሻል፣
· ጥገና ክፍሉ በመሳሪያዎች፣ በመፍቻዎች ልዩ የጥገና ማሽኖች በማሰባሰብ የጥገና ክፍሉን ያሟላል፣
· ለጋራዡ የሚያስፈልጉ የመለዋወጫ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ዝርዝር በማውጣት እንዲገዙ ያደርጋል፣
· ከስቶክ ከማለቃቸው በፊት እንዲተኩ የዕቃ መጠየቂያ ሞልቶ ለሚመለከተው ያቀርባል፣
2. የድርጅቱ ተሸከርካሪዎችና ማሽነሪዎች በቂ ክትትል ያደርጋል፤
· የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች በየወቅቱ ፍተሻ እንዲደረግላቸውና በጥንቃቄ እንዲያዙ ያደርጋል፣
· በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ለሥራ ከመሰማራታቸው በፊት ፍተሻ ያደርጋል፣
· የተሽከርካሪዎች ጽዳት እንዲጠበቅ መመሪያ ይሰጣል፣
· በወቅቱ ሰርቪስ መደረጋቸውንና የተለያዩ መሟላት ያለባቸው ዕቃዎችና መሳሪያዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣
· መለዋወጫዎች ከመገጠማቸው በፊት ዓይነታቸው፣ ጥራታቸውና መጠናቸው ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጣል፣
· ለጥገና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን ያረጋግጣል፣
· የድርጅቱ ተሸከርካሪዎች ማሽነሪዎች ብልሽት ሲያጋጥማቸው አስፈላጊውን ጥገና ያደርጋል፣
· ሾፌሮች የሚያቀርቡትን የጥገና ጥያቄ በመነሳት የብልሽት መንስኤዎችን ይመረምራል፣ ለአስተዳደር ኃላፊው ያማክራል፣
· ከአቅም በላይ የሆነ ብልሽት ሲያጋጥመው ሪፖርት ያደርጋል፣
· ከድርጅቱ ውጪ የሚደረጉ ጥገናዎችን በየዕለቱ ይከታተላል፣ የሚያስፈልገውን መለዋወጫ ያቀርባል፣
· መሳሪያዎች በኦፕሬተሮቻቸው በቂ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው ይከታተላል፣
3. የተሸከርካሪና የማሽነሪ አጠቃቀም ይከታተላል፣ ያስተምራል፤
· የተሸከርካሪና የማሽነሪ አጠቃቀም ያስተምራል፣ እንደ አስፈላጊነቱ መለስተኛ ማሽነሪዎች /Mixer, Vibrator, Water pump, Compactor, HCB Machine, etc…/ ስልጠና ይሰጣል፣
· ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ማሽነሪ የጥገና ታሪክ መከታተያ ማህደር ያዘጋጃል፣
· የደህንነት አጠባበቅ የነዳጅ ፍጆታን ለመቆጣጠር ሾፌሮችን ያማክራል፣
· ድርጅቱ ለወጪ እንዳይጋለጥ ጥገናዎች በተቻለ አቅም በድርጅቱ ጥገና ክፍል እንዲጠናቀቁ ይመክራል፣
· በተሽከርካሪዎች ላይ የእሳት ማጥፊያ እንዲቀመጥ ያደርጋል፣ አጠቃቀሙን ያሰለጥናል፣
· የተሽከርካሪዎች መውጫና የዓመታዊ ምርመራ ይከታተላል፣ እንዲፈጸም ያደርጋል፣
4. ስለሥራው ሁኔታ በየጊዜው ሪፖርት ያደርጋል፤
· የተሸከርካሪዎችን የጥገና የሰርቪስ እና የነዳጅና የዘይት ፍጆታ አጠቃላይ ሪፖርት ያዘጋጃል፣
· የተሽከርካሪዎችን ሁኔታ እየተከታተለ ዝርዝር ሁኔታቸውን በመመርመር አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሪፖርት ያቀርባል፣
· የመሳሪያዎችን ወርሃዊና ዝርዝር ሁኔታ ያቀርባል፣
· የኢንሹራንስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ተሽከርካሪዎችን ማሽነሪዎች ጉዳይ በወቅቱ ለሚመለከተው ክፍል/ሠራተኛ ሪፖርት ያደርጋል፣
· ለተሰራው ሥራ የዋጋ ተመን በማውጣት፣ የተሰራውን ሥራና የወጣውን ወጪ በማነጻጸር ተገቢውን አስተያየት ይሰጣል፣
5. በተጨማሪም ከቅርብ ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
እኔ የድርጅቱ ሠራተኛ ስሆን፤ ከዚህ በላይ በተሰጠኝ ኃላፊነትና የሥራ መደብ ዝርዝር መሠረት ለመስራት ተስማምቻለሁ፡፡
ማስገንዘቢያ ፡ - ከላይ የሰፈሩት የሥራ ዝርዝሮች ላይ የተጻፉት ቃላት/ዓረፍተ-ነገሮች ለሁለቱም ጾታዎች (ለወንድም ለሴትም) ያገለግላሉ፡፡